Thursday, October 23, 2025

የ5ቱ “ማ” ዎች ትግበራ በድሬ ጠ ያራ ወረዳ 

#HMKI ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም፡ የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የሰራተኞችን የስራ ሞራል በማነሳሳት እና የጋራ ስራን በማበረታታት የባለቤትነት ስሜትን ለመፍጠር የ5ቱ “ማ” ዎችን በተሟላ መልኩ መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።

በመርሃ ግብሩ በተቀመጠው የትግበራ ፕሮግራም መሠረት በወረዳው መስተዳደር የሚገኘው ንብረት ክፍል 5ቱ "ማ" ዎችን ለመተግበር የልየታ ሥራ በማከናወን፣ የ5ቱ "ማ" ዎች የመጀመሪያው "ማ" (ማጣራት) ሥራ እየተከናወነ ሲሆን፣ በዚህ ሂደት የሚያስፈልጉ ቁሶችን እና የማያስፈልጉ ቁሶችን ለመለየት፣ አፋጣኝ እልባት የሚሹትን ቁሶች (መድኃኒቶች) በቅድሚያ እንዲለዩ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

የካይዘን ከፍተኛ ኤክስፐርት የሆኑት አቶ ኻሊድ ዜይዳን እንደገለፁት “ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአፋጣኝ እንዲወገዱ የተደረጉት በዋነኛነት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የተለያዩ የእንስሳት ህክምና መድኃኒቶች ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመነጋገር በዘርፉ ባለሙያ እገዛ እንዲወገዱ ተደርጓል። በቀጣይም ሌሎች ቁሳቁሶችን በመርሃግብሩ መሰረት የሚከናወኑ መሆኑን አቶ ኻሊድ ገልፅዋል።"

ይህ ትግበራ ቀደም ሲል መስከረም 07 ቀን 2018 ዓም በኢንስቲትዩት እና በወረዳ መስተዳደሩ መካከል በተፈረመ የመግባቢያ ሰነድ ከተካተቱ የትኩረት መስኮች ውስጥ አንዱ የካይዘን ሥልጠና እና ትግበራ አካል መሆኑን ይታወሳል።
የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች

      

    
                            

Tuesday, September 10, 2024

Monday, September 9, 2024

የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳት ምረቃ

 #HMKI ጳጉሜን 4 /2016 ዓም

ሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት በአቦከር ወረዳ የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳት ያደረገውን ቤት ተጠናቆ ለባለቤቱ አስረከበ::





Thursday, September 5, 2024

"ጳጉሜን ለኢትዮጵያ"

#HMKI ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓም፡-

ሀረሪ ሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት በተቋሙ አዳራሽ ከኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ምⷍክር ተደረገ።

ምክⷍር መድረኩ በ2016 አመት ማጠናቀቂያ የጳጉሜን 1 እስከ 5 ቀናት በሚካሄዱ ሁነቶች ላይ በኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ሁሉም አመራሮችና ሰራተኞች በነቂስ እንዲሳተፉ አሳስበዋል።


 

"ከልቡ" ትግበራ ሥልጠና

#HMKI ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓም፡-

ሀረሪ ሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት የሰራተኞችን አቅም ለመገንባት በተቋሙ አዳራሽ የካይዘን ልማት ቡድን አሰራርና አተገባበር ላይ ሥልጠና እና ከኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ምⷍክር ተደረገ።




ምክⷍር መድረኩ በ2016 አመት ማጠናቀቂያ የጳጉሜን 1 እስከ 5 ቀናት በሚካሄዱ ሁነቶች ላይ በኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ሁሉም አመራሮችና ሰራተኞች በነቂስ እንዲሳተፉ አሳስበዋል።

በመቀጠልም ሥልጠናው በኢንስቲትዩቱ ሥራ አመራር አገልግሎት ዳይሬክተር እና በጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ዳይሬክተር ጋር በመሆን ከልቡ (ካይዘን ልማት ቡድን) አመሰራረትና አተገባበር ዙሪያ የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ሥልጠና በመስጠት ቀጣይነት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማጎልበት ከፍተኛ ዕገዛ ያለው በመሆኑ በየጊዜው በተያዘው እቅድ መሰረት ስልጠናው የሚሰጥ ሲሆን በመግለጽ፣ በኢንስቲትዩቱ የተቋቋሙ የካይዘን ልማት ቡድኖችን በማነቃቃት ትግበራው በተደራጀ መልኩ እንዲከናወን ለማድረግ የታለመ ስልጠና መሆኑን ስልጠናው ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። በመሆኑም ነሐሴ 30/ 2016 ዓም ለአንድ ቀን ሲሰጥ የነበረው “ከልቡ” የአቅም ግንባታ ሥልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ።



የ5ቱ “ማ” ዎች ትግበራ በድሬ ጠ ያራ ወረዳ  #HMKI ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም፡ የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የ...