#HMKI ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓም፡-
ሀረሪ ሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት የሰራተኞችን አቅም ለመገንባት በተቋሙ አዳራሽ የካይዘን ልማት ቡድን አሰራርና አተገባበር ላይ ሥልጠና እና ከኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ምⷍክር ተደረገ።
ምክⷍር መድረኩ በ2016 አመት ማጠናቀቂያ የጳጉሜን 1 እስከ 5 ቀናት በሚካሄዱ ሁነቶች ላይ በኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ሁሉም አመራሮችና ሰራተኞች በነቂስ እንዲሳተፉ አሳስበዋል።
በመቀጠልም ሥልጠናው በኢንስቲትዩቱ ሥራ አመራር አገልግሎት ዳይሬክተር እና በጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ዳይሬክተር ጋር በመሆን ከልቡ (ካይዘን ልማት ቡድን) አመሰራረትና አተገባበር ዙሪያ የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ሥልጠና በመስጠት ቀጣይነት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማጎልበት ከፍተኛ ዕገዛ ያለው በመሆኑ በየጊዜው በተያዘው እቅድ መሰረት ስልጠናው የሚሰጥ ሲሆን በመግለጽ፣ በኢንስቲትዩቱ የተቋቋሙ የካይዘን ልማት ቡድኖችን በማነቃቃት ትግበራው በተደራጀ መልኩ እንዲከናወን ለማድረግ የታለመ ስልጠና መሆኑን ስልጠናው ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። በመሆኑም ነሐሴ 30/ 2016 ዓም ለአንድ ቀን ሲሰጥ የነበረው “ከልቡ” የአቅም ግንባታ ሥልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ።
Comments
Post a Comment