Sunday, January 15, 2023

Microsoft Excel Sheet


Microsoft Excel Sheet

Microsoft Excel Sheet ላይ ለምሳሌ ስምና የአባት ስም በተለያዩ cell ላይ የተቀመጠውን በአንድ ሴል ላይ ማስቀመጥ ብልፈልግ CONCATENATE የሚባለውን ፈንክሽን በመጠቀም መስራት ይቻላል

ለምሳሌ Excel Sheet ላይ ስም A2 ላይ የአባት ስም B2 ላይ ቢቀመጥ በአንድ ላይ C2 ላይ ማስቀመጥ ብፈልግ C2 ላይ = CONCATENATE (B2, A2) ብለን በመጻፍ ሁለቱን በአንድ ላይ ያደርግልናል። ግን በስምና በአባት ስም ላይ ምንም ክፍተት አይኖረውም። እንዲኖረው ከተፈለገ = CONCATENATE (A2," ", B2) ብለን መጻፍ ይጠበቅብባል " " ይህ ኮቴሽን መቀመጡ በስምና በአባት ስም ክፍተት እንዲኖር ያደርጋል። 

ሌላው ስምና የአባት ስምን በማገናኘት ኢሜይል ማዘጋጀት ብንፈልግ = CONCATENATE (A2, B2,"@gmail.com") ብለን በመጻፍ excel ላይ ያለውን ሁሉንም ስምና የአባት ስም በአንድ ላይ በማገናኘት @gmail.com የሚለውን በመጨመር ያዘጋጅልናል ማለት ነው። ቅድሚያ እንዴት አድርገን MS Excel መክፈት እንችላለን የሚለውን እንመልከት።

በመጀመሪያ Windows 7,8,1 0,11 የምትጠቀሙ ከሆናችሁ መፈለጊያ(Search) ማድረጊያው ላይ Excel ብላችሁ ፈልጉ ከዛም MS Excel ይመጣላችኋል ከዛም Click በማድረግ ይክፈቱት።

መልካም አሁን excel የመስሪያ ገጽ ይመጣላችኋል ሰንጠረዥ  በሆነ መልኩ ማለት ነው። እንደምታዩት ሰንጠረዡ ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ የተዘረዘሩ A, B, C, D, E, F... እያለ የሚሄድ ሲሆን ከግራ በኩል ወደ ታች ደግሞ 1,2,3,4,5...እያለ ይሄዳል ማለት ነው።

ስለዚህ አሁን ማወቅ ያለባችሁ ጉዳይ ምንድን ነው በሂሳብ ትምህርት X, Y Coordinate የሚባለው የXና የY መገናኛ ቦታ ማለት ነው። ከላይ የጠቀስኩት ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ A, B, C, D, E, F...እና ከግራ ከላይ ወደ ታች የተዘረዘረ 1,2,3,4,5...እያለ የሚሄደው ቁጥር የሚገናኙበት አንዷ ሰንጠረዥ Cell ትባላለች እናም በዚህች Cell የሚቀመጥ ማንኛውም ቁጥር፣ ጽሁፍ፣ ምልክቶች Values ይባላሉ። 

የሚገኑበት ቦታ ደግሞ ለምሳሌ ከExcel የመጀመሪያው Cell ላይ መገኛ A1 ይባላል ይህ ማለት Value የተቀመጠበትን ቦታ (Coordinate) ማየት ይጠበቅብናል ማለት ነው ስለዚህ ለምሳሌ A5 ሊሆን ይችላል F27 ሊሆን ይችላል ማለት ነው። ይህንን ካወቅን ወደሚቀጥለው እንሂድ።

የExcel_Functions

1ኛ SUM የሚባለው Function በExcel ላይ ያሉትን Cell Values ለመደመር የሚያገለግለን ነው። ለምሳሌ የሆነ Cell ላይ በማስቀመጥ ወይም E9 ላይ በማድረግ =SUM (E4:E8) የሚለውን ከጻፍን ከE4 እስከ E8 ድረስ ያለውን ይደምርልናል ማለት ነው።

    =SUM (E4, E8) ብለን ከጻፍን E4 እና E8 ብቻ ይደምርልናል።
    =SUM (E4:E8)/5 የሚለውን ከጻፍን ከE4 እስከ E8 ድረስ ያለውን ይደምርና ከ5 በማካፈል አማካይ ውጤት ያስቀምጥልናል         ማለት ነው።

    =SUM (E4, E8)/2 ብለን ከጻፍን E4 እና E8 ብቻ ይደምርና ለ2 በማካፈል አማካይ ውጤት ያስቀምጥልናል።

2ኛ AVERAGE Function ይህ Function Excel ላይ አማካይ ውጤትን ለመስራት ይጠቅመናል። ለምሳሌ ከB2 ጀምሮ እስከ B6 ድረስ ቁጥር Values ብናስገባና የሆነ Cell ላይ ወይም B7 ላይ በማስቀመጥ  ይህንን ብንጽፍ =AVERAGE (B2:B6) የሚለውን ከጻፍን ከB2 እስከ B6 ድረስ ያለውን Average አማካይ ውጤት ይሰጠናል ማለት ነው።

3ኛ MIN Function ይህ Function Excel ላይ ዝቅተኛ ውጤትን ለማወቅ ይጠቅመናል። ለምሳሌ ከB2 ጀምሮ እስከ B6 ድረስ ቁጥር Values ብናስገባና የሆነ Cell ላይ ወይም B7 ላይ በማስቀመጥ  ይህንን ብንጽፍ =MIN (B2:B6) የሚለውን ከጻፍን ከB2 እስከ B6 ድረስ ያለውን ዝቅተኛ ውጤት(ቁጥር ያለውን) ይሰጠናል ማለት ነው።

4ኛ MAX Function ይህ Function Excel ላይ ከፍተኛ ውጤትን ለማወቅ ይጠቅመናል። ለምሳሌ ከB2 ጀምሮ እስከ B6 ድረስ ቁጥር Values ብናስገባና የሆነ Cell ላይ ወይም B7 ላይ በማስቀመጥ  ይህንን ብንጽፍ = MAX (B2:B6) የሚለውን ከጻፍን ከB2 እስከ B6 ድረስ ያለውን ከፍተኛ ውጤት(ቁጥር ያለውን) ይሰጠናል ማለት ነው።

5ኛ COUNT Function ይህ Function Excel ላይ የCell ብዛትን ለማወቅ ይጠቅመናል። ለምሳሌ ከB2 ጀምሮ እስከ B6 ድረስ ቁጥር Values ብናስገባና የሆነ Cell ላይ ወይም B7 ላይ በማስቀመጥ  ይህንን ብንጽፍ =COUNT (B2:B6) የሚለውን ከጻፍን ከB2 እስከ B6 ድረስ ያለውን  Number of Cell በቁጥር ያስቀምጥልናል ስለዚህ መልሱ 5 የሚል መልስ ይሰጠናል ማለት ነው።

6ኛ LEN Function ይህ Function Excel ላይ Number of characters ወይም Number of spellings ብዛትን ለማወቅ ይጠቅመናል። ለምሳሌ B2 ላይ ያለውን ያዳታ Character ብዛት ለማወቅ ብንፈልግ  B3 ላይ ወይም ሌላ Cell ላይ በማስቀመጥ  ይህንን ብንጽፍ =LEN(B2) የሚለውን ከጻፍን B2  ላይ ያለው መረጃ MUHAMMED ቢሆን Muhammed የሚለውን በመቁጠር በቁጥር 8 ብሎ ያስቀምጥልናል ምክንያቱም Muhammed የሚለው Number of characters ብዛት 8 ስለሆነ ማለት ነው።

6ኛ በተጨማሪም ለመደመር፣ ለመቀነስ፣ ለማካፈል፣ ለማባዛት የሚከተለውን አጭር መንገድ ተከተሉ።

ለምሳሌ: B2, C2, D2, E2, F2 ላይ የተቀመጡ ቁጥሮች ቢኖሩ ከB2 እስከ F2 ያለውን ቁጥር ለመደመር ብንፈልግ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ ባለው መልክ መስራት ትችላላችሁ እንደ አማራጭ ግን
  1. ምሳሌ G2 ላይ በማስቀመጥ ከርሰራችሁን =B2+C2+D2+E2+F2 ብላችሁ ኢንተርን ብትጫኑ ከB2 እስከ F2 ድረስ ያለው ይደምርና ድምሩን G2 ላይ ያስቀምጣል ማለት ነው።
  2. ለማባዛት ብትፈልጉ ለምሳሌ B2 ና C2 ማባዛት ብትፈልጉ የሆነ cell ላይ ከርሰራችሁን በማስቀመጥ =B2*C2 በማለት ከዛም ኢንተርን ስትጫኑ የB2ንና C2ና ዋጋ በማባዛት ያስቀምጥላችኋል ማለት ነው።
  3. ማላፈልና መቀነስ ልክ እንደ ማባዛቱ የ* በመቀየር / ወይም - መጠቀም ትችላላችሁ።

#ያወቁትንማሳወቅብልህነትነው!

Source: https://t.me/MuhammedComputerTechnology

1 comment:

የ5ቱ “ማ” ዎች ትግበራ በድሬ ጠ ያራ ወረዳ  #HMKI ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም፡ የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የ...