Tuesday, September 29, 2026

“የመንግሥት ሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና የአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋይ አያያዝ”


#HMKI መስከረም 19 ቀን 2019 ዓም

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መውሰድ ጀመሩ!

የሀረሪ ክልል ሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት-ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሥልጠና በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

የሥልጠናው ዋና ትኩረት፦ “የመንግሥት ሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና የአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋይ አያያዝ”

 የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰላሃዲን ቶውፊቅ ሥልጠናውን በይፋ በከፈቱበት ወቅት እንዳሳሰቡት፤ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጣ ማንኛውም ተገልጋይ ፍትሃዊ፣ ፈጣን እና በአክብሮት የታጀበ አገልግሎት የማግኘት መብት አለው። ይህ ሥልጠናም የሠራተኞችን ሙያዊ ሥነ-ምግባር በማሳደግ የፍትህ አገልግሎቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። ሲሉ ስልጠናው በይፋ መከፈቱን አብስረዋል።

ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ የፍርድ ቤቱ ሠራተኞች የሚሳተፉበት ይህ ሥልጠና ከመስከረም 19 ቀን እስከ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓም ድረስ ለአራት ተከታታይ ቀና የሚቆይ ይሆናል።






ቅታዊና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት:

በዌብሳይት: Blog

https://www.hmkimedia.blogspot.com/

በYoutube ቻነላችን

https://youtube.com/@hmkimedia

በቴሌግራም:

https://t.me/c/1260317423/383

በፌስቡክ:

https://www.facebook.com/hararimanagement.andkaizeninstitute

በፌስቡክ ገፃችን:

https://www.facebook.com/hararimki

በትዊተር፣

https://twitter.com/hararimki?t=j8vGvcUAHxwcw1Sjba3JMA&s=09

ተቀላቀሉን!!! 





Thursday, September 24, 2026

የ5ቱ ማዎች የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence – EI)

#HMKI መስከረም 13 ቀን 2019 ዓም “የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የሰራተኞችን የስራ ሞራል በማነሳሳት እና የጋራ ስራን በማበረታታት የባለቤትነት ስሜትን ለመፍጠር የ5ቱ “ማ” ዎችን በተሟላ መልኩ መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።

ስልጠናው በዘጠኙም ወረዳዎች ለሚገኙ የንብረት ክፍል፣ የመዝገብ ቤት እና የሰው ኃይል ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠናው ዓላማ፥ ብክነትን በመከላከል ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለመፍጠር እንዲሁም ስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence – EI) በተመለከተም ሰልጣኞች የራሳቸውና የሌሎችን ስሜት በመለየት፣ በመረዳት፣ በመቆጣጠር እና ስሜታቸውን በተገቢ መንገድ በመጠቀም ጤናማ ግንኙነትና ውጤታማ ውሳኔ መስጠት እንድችሉ ለማድረግ የታለመ ስልጠና ነው።

የስራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት በክልሉ ለሚገኙ 9 ወረዳዎች በከይዘን ፍልስፍና አመራር "5ቱ ማ"ዎች እና "የስሜት ብልህነት"ዙሪያ ለአንድ ቀን ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ ተሰጠ።

መስከረም 13 ቀን 2019 ዓም






Wednesday, September 23, 2026

 

#HMKI መስከረም 12 ቀን 2019 ዓም የስራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት በክልሉ ለሚገኙ ሴክተር ተቋማት፥ በከይዘን ፍልስፍና አመራር "5 ማ"ዎችን እና "የስሜት ብልህነት"ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

ስልጠናው ለንብረት ክፍል፣ መዝገብ ቤት እና ለሰው ኃይል ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠናው ዓላማ፥ ብክነትን በመከላከል ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለመፍጠር እንዲሁም ስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence – EI) በተመለከተም ሰልጣኞች የራሳቸውና የሌሎችን ስሜት በመለየት፣ በመረዳት፣ በመቆጣጠር እና ስሜታቸውን በተገቢ መንገድ በመጠቀም ጤናማ ግንኙነትና ውጤታማ ውሳኔ መፍጠር እንድችሉ ለማድረግ የታለመ ስልጠና ነው። ስልጠናው በቀጣይም ለሌሎች ተቋማት የሚሰጥ ይሆናል።





Wednesday, February 11, 2026

የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳት

 HMKI ታህሳስ 4 /2018 ዓም

ሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት በአሚር ኑር ወረዳ የአቅመ ደካማ ቤት: 300 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ዕድሳቱን አጠናቆ ቤቱን ለወረዳው አስረከበ::



Thursday, October 23, 2025

የ5ቱ “ማ” ዎች ትግበራ በድሬ ጠ ያራ ወረዳ 

#HMKI ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም፡ የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የሰራተኞችን የስራ ሞራል በማነሳሳት እና የጋራ ስራን በማበረታታት የባለቤትነት ስሜትን ለመፍጠር የ5ቱ “ማ” ዎችን በተሟላ መልኩ መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።

በመርሃ ግብሩ በተቀመጠው የትግበራ ፕሮግራም መሠረት በወረዳው መስተዳደር የሚገኘው ንብረት ክፍል 5ቱ "ማ" ዎችን ለመተግበር የልየታ ሥራ በማከናወን፣ የ5ቱ "ማ" ዎች የመጀመሪያው "ማ" (ማጣራት) ሥራ እየተከናወነ ሲሆን፣ በዚህ ሂደት የሚያስፈልጉ ቁሶችን እና የማያስፈልጉ ቁሶችን ለመለየት፣ አፋጣኝ እልባት የሚሹትን ቁሶች (መድኃኒቶች) በቅድሚያ እንዲለዩ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

የካይዘን ከፍተኛ ኤክስፐርት የሆኑት አቶ ኻሊድ ዜይዳን እንደገለፁት “ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአፋጣኝ እንዲወገዱ የተደረጉት በዋነኛነት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የተለያዩ የእንስሳት ህክምና መድኃኒቶች ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመነጋገር በዘርፉ ባለሙያ እገዛ እንዲወገዱ ተደርጓል። በቀጣይም ሌሎች ቁሳቁሶችን በመርሃግብሩ መሰረት የሚከናወኑ መሆኑን አቶ ኻሊድ ገልፅዋል።"

ይህ ትግበራ ቀደም ሲል መስከረም 07 ቀን 2018 ዓም በኢንስቲትዩት እና በወረዳ መስተዳደሩ መካከል በተፈረመ የመግባቢያ ሰነድ ከተካተቱ የትኩረት መስኮች ውስጥ አንዱ የካይዘን ሥልጠና እና ትግበራ አካል መሆኑን ይታወሳል።
የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች

      

    
                            

Tuesday, September 10, 2024

“የመንግሥት ሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና የአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋይ አያያዝ” #HMKI መስከረም 19 ቀን 2019 ዓም የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መውሰድ ጀመሩ! የሀረሪ ክል...