የ2017 በጀት ዓመት
የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ
#HMKI ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም
በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል
እንዲሁም የታዩ ጉድለቶችን በማረም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።
የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት
ዓመት የመደበኛ ዕቅድ የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት (የ6 ወር) ዕቅድ አፈፃፀምን በሚመለከት ከኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ጋር በመሆን
የአፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።
ግምገማው የ2017 በጀት ዓመት በ1ኛው መንፈቅ
ዓመት (የ6 ወር) ዕቅድ አፈፃፀም የተከናወኑ ቁልፍ ተግባራት ላይ በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጉድለቶችን፣ ጠንካራ ጎኖችን እንዲሁም
ያጋጠሙ ችግሮችን የገመገመ ሲሆን፣ ጉድለቶችን በማረም እና የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በቀጣይ ሊስተካከሉ የሚገባቸውን በመለየት፣
በቀጣይ የተሻለ የአፈጻጸም ውጤት ለማምጣት ሁሉም የተቋሙ ሰራተኛ ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
በመጨረሻም ጥር 5 ቀን 2017 ዓም ለግማሽ
ቀን በኢንስቲትዩቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የአፈፃፀም ግምገማ ተጠናቋል።
በርቱ
ReplyDelete