Thursday, October 23, 2025

የ5ቱ “ማ” ዎች ትግበራ በድሬ ጠ ያራ ወረዳ 

#HMKI ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም፡ የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የሰራተኞችን የስራ ሞራል በማነሳሳት እና የጋራ ስራን በማበረታታት የባለቤትነት ስሜትን ለመፍጠር የ5ቱ “ማ” ዎችን በተሟላ መልኩ መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።

በመርሃ ግብሩ በተቀመጠው የትግበራ ፕሮግራም መሠረት በወረዳው መስተዳደር የሚገኘው ንብረት ክፍል 5ቱ "ማ" ዎችን ለመተግበር የልየታ ሥራ በማከናወን፣ የ5ቱ "ማ" ዎች የመጀመሪያው "ማ" (ማጣራት) ሥራ እየተከናወነ ሲሆን፣ በዚህ ሂደት የሚያስፈልጉ ቁሶችን እና የማያስፈልጉ ቁሶችን ለመለየት፣ አፋጣኝ እልባት የሚሹትን ቁሶች (መድኃኒቶች) በቅድሚያ እንዲለዩ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

የካይዘን ከፍተኛ ኤክስፐርት የሆኑት አቶ ኻሊድ ዜይዳን እንደገለፁት “ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአፋጣኝ እንዲወገዱ የተደረጉት በዋነኛነት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የተለያዩ የእንስሳት ህክምና መድኃኒቶች ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመነጋገር በዘርፉ ባለሙያ እገዛ እንዲወገዱ ተደርጓል። በቀጣይም ሌሎች ቁሳቁሶችን በመርሃግብሩ መሰረት የሚከናወኑ መሆኑን አቶ ኻሊድ ገልፅዋል።"

ይህ ትግበራ ቀደም ሲል መስከረም 07 ቀን 2018 ዓም በኢንስቲትዩት እና በወረዳ መስተዳደሩ መካከል በተፈረመ የመግባቢያ ሰነድ ከተካተቱ የትኩረት መስኮች ውስጥ አንዱ የካይዘን ሥልጠና እና ትግበራ አካል መሆኑን ይታወሳል።
የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች

      

    
                            

No comments:

Post a Comment

የ5ቱ “ማ” ዎች ትግበራ በድሬ ጠ ያራ ወረዳ  #HMKI ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም፡ የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የ...