Wednesday, January 3, 2024

የ2016 በጀት ዓመት 1ኛው መንፈቅ ዓመት (የ6 ወር) ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ

የ2016 በጀት ዓመት 

የ1ኛው መንፈቅ ዓመት (የ6 ወር) ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ 


#HMKI ታህሳስ 24 ቀን 2016 .

በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እንዲሁም የታዩ ጉድለቶችን በማረም ተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ።

የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት 2016 በጀት ዓመት የመደበኛ ዕቅድ የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት (የ6 ወር) ዕቅድ አፈፃፀምን በሚመለከት ከኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ጋር በመሆን የአፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

ግምገማው 2016 በጀት ዓመት 1ኛው መንፈቅ ዓመት (የ6 ወር) ዕቅድ አፈፃፀም የተከናወኑ ቁልፍ ተግባራት ላይ በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጉድለቶችንጠንካራ ጎኖችን እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን የገመገመ ሲሆንጉድለቶችን በማረም እና የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በቀጣይ ሊስተካከሉ የሚገባቸውን በመለየት በቀጣይ የተሻለ የአፈጻጸም ውጤት ለማምጣት ሁሉም የተቋሙ ሰራተኛ ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። 

በመቀጠል ታህሳስ 25 ቀን 2016 ዓም የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞች በጊዜ ሥራ አመራር /Time Management/ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠናም ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የላቀ አፈፃፀም ውጤት ላስመዘገቡ የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞችም እውቅና በመስጠት፣ ታህሳስ 24 -25 ቀን 2016 ዓም ለሁለት ቀን በኢንስቲትዩቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የአፈፃፀም ግምገማ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የእውቅና ፕሮግራም ተጠናቋል።





No comments:

Post a Comment

የ5ቱ “ማ” ዎች ትግበራ በድሬ ጠ ያራ ወረዳ  #HMKI ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም፡ የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የ...