ካይዘን አመራር ፍልስፍና - ሥልጠና

ካይዘን አመራር ፍልስፍና - ሥልጠና 


#HMKI ታህሳስ 21 ቀን 2015 የሀረሪ ክልል ስራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት ከሀረሪ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በካይዘን አመራር ፍልስፍና ዙሪያ በክልሉ ለሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና ንብረት ክፍል ኃላፊዎች በኢንስቲትዩቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በሥልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀረሪ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ፈሪሃ መሀመድ እንዳሉት “ከይዘን በክልላችን መተግበር የሚያስገኘውን ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ውስጥ ቀጣይነት ያለው ውጤታማነት፣ ከብክነት የፀዳ ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ፍልስፍና በመሆኑ፣

ይህን የለውጥ መሳሪያ በተቀናጅና በዕውቀት ተግባራዊ ለማድረግ በተመረጡ የትምህርት ተቋማት ሥልጥናው እንዲሰጥ የተደረገ መሆኑን እና በቀጣይ ሌሎች ተቋማት ላይም መሰል ሥልጠናዎች እንደሚሰጥ፣ በቀጣይ ኢንስቲትዩቱ በክልሉ ከይዘንን ውጤታማ አድርጎ ለማስቀጠል ለተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁ ሲሆን፣ በዚህ የሁለት ቀናት የሥልጠና ቆይታችሁ ወቅት ሥልጠናውን በንቃት እንድትከታተሉ” በማለት ሥልጠናው መከፈቱን አብስረዋል። ሥልጠናው ከታህሳስ 21ቀን እስከ ታህሳስ 22/2015ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

ወቅታዊና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት:

Blogspot:
https://hmkimedia.blogspot.com/

YouTube ቻነላችን:
https://youtube.com/channel/UCYBkzF7_NRvlk6OvMrNVIrQ

በቴሌግራም:
https://t.me/c/1260317423/383

በፌስቡክ:
https://www.facebook.com/hararimanagement.andkaizeninstitute

በፌስቡክ ገፃችን:
https://www.facebook.com/hararimki

ተቀላቀሉን



ክብርት ወ/ሮ ፈሪሃ መሀመድ
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ ኃላፊ




ሠልጣኖች



Post a Comment

4 Comments