Tuesday, January 3, 2023

BIG CLEANING DAY

Creating a Conducive and Clean Working Environment is inevitable !!



#HMKI ህዳር 07 ቀን 2016 ዓ.ም የፅዳት ቀን!


በአንድ ህንፃ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት ማለትም የስራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት፣ የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ፣ እንዲሁም ማህበራት ማደራጃ ኤጀንሲ ተቋማት፣ ከተቋማቱ ሠራተኞች ጋር በመሆን “ታላቅ የፅዳት ቀን/ Big Cleaning Day“ በሚል መሪ ቃል ተቋማቱ የሚገኙበትን ግቢ እና አካባቢውን ፅዱና ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር አጋዥ በሆነው የካይዘን መራጃ /Tool 5ቱ 'ማ’ ዎች ውስጥ 3ኛውን “የማፅዳት” ተግባርን በመጠቀም በኢንስቲትዩቱ አስተባባሪነት ህዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ።
የፅዳት ዘመቻው ተቋማት የሚሰሩበትን የሥራ አካባቢ ፅዱ፣ ምቹና ማራኪ ማድረግ የሥራ ተነሳሽነትን ለማጎልበት የላቀ ሚና ስለሚኖረው፣ የፅዳት ዘመቻ ፕሮግራሙ ህዳር ወር እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዘውትር ዓርብ ቀን የሚቀጥልና የሚተገበር ይሆናል።






1 comment:

የ5ቱ “ማ” ዎች ትግበራ በድሬ ጠ ያራ ወረዳ  #HMKI ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም፡ የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የ...