Thursday, October 8, 2026

 đŸšŚ ለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በስሜታዊ ብልህነት ስልጠና መስጠት ተጀመረ

#HMKI

መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም

ለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በ“ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)” ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ

የሥራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት (HMKI) ከሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር “ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)” በሚል ርዕስ ለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ስልጠናው የትራፊክ ፖሊስ አባላትና አመራሮችን በሶስት ሺፍት በመከፋፈል፣ ከመስከረም 28–30 ቀን 2019 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

የስልጠናው ዋና ዓላማ የትራፊክ ፖሊስ አባላትና አመራሮች የራሳቸውን ስሜት በመረዳትና በመቆጣጠር፣ የሌሎችን ስሜት በመረዳት እና በተገቢ ሙያዊ መንገድ ምላሽ በመስጠት ውጤታማ፣ ሰው-ተኮር እና ሙያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ አቅም ማጎልበት ነው።

ስሜታዊ ብልህነት በተለይ አስጨናቂና በአስቸጋሪ የሥራ ሁኔታዎች ውስጥ ራስን መቆጣጠር፣ ግጭትን በአግባቡ መፍታት፣ ከሕዝብ ጋር በአክብሮት መግባባት እና በሙያዊ ሥነ-ምግባር ሥራን ማከናወን ላይ ወሳኝ ሚና አለው።

HMKI — አቅምን መገንባት ለተሻለ አፈፃፀም!

#HMKI #Emotional_Intelligence #Traffic_Police #Capacity_Building #Harari_Police_Commission #ስሜታዊ_ብልህነት #የትራፊክ_ፖሊስ #አቅም_ግንባታ










No comments:

Post a Comment

  # HMKI  ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ . ም በስሜታዊ ብልህነትና በካይዘን 5S ትግበራ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ የሥራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት ( HMKI ) ከሀረሪ  ጉባ...