#HMKI መስከረም 19 ቀን 2019 ዓም
የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና
መውሰድ ጀመሩ!
የሀረሪ ክልል ሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት-ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሥልጠና በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።
የሥልጠናው ዋና ትኩረት፦ “የመንግሥት ሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና የአገልግሎት አሰጣጥና
የተገልጋይ አያያዝ”
የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰላሃዲን ቶውፊቅ ሥልጠናውን በይፋ በከፈቱበት ወቅት እንዳሳሰቡት፤ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጣ ማንኛውም ተገልጋይ ፍትሃዊ፣ ፈጣን እና በአክብሮት የታጀበ አገልግሎት የማግኘት መብት አለው። ይህ ሥልጠናም የሠራተኞችን ሙያዊ ሥነ-ምግባር በማሳደግ የፍትህ አገልግሎቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። ሲሉ ስልጠናው በይፋ መከፈቱን አብስረዋል።
ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ የፍርድ
ቤቱ ሠራተኞች የሚሳተፉበት ይህ ሥልጠና ከመስከረም 19 ቀን እስከ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓም ድረስ ለአራት ተከታታይ ቀና የሚቆይ ይሆናል።






No comments:
Post a Comment