የ5ቱ ማዎች የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence – EI)
#HMKI መስከረም 13 ቀን 2019 ዓም “የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የሰራተኞችን የስራ ሞራል በማነሳሳት እና የጋራ ስራን በማበረታታት የባለቤትነት ስሜትን ለመፍጠር የ5ቱ “ማ” ዎችን በተሟላ መልኩ መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።
ስልጠናው በዘጠኙም ወረዳዎች ለሚገኙ የንብረት ክፍል፣ የመዝገብ ቤት እና የሰው ኃይል ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠናው ዓላማ፥ ብክነትን በመከላከል ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር
ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለመፍጠር እንዲሁም ስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence – EI) በተመለከተም ሰልጣኞች
የራሳቸውና የሌሎችን ስሜት በመለየት፣ በመረዳት፣ በመቆጣጠር እና ስሜታቸውን በተገቢ መንገድ በመጠቀም ጤናማ ግንኙነትና ውጤታማ
ውሳኔ መስጠት እንድችሉ ለማድረግ የታለመ ስልጠና ነው።
የስራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት በክልሉ ለሚገኙ 9 ወረዳዎች በከይዘን
ፍልስፍና አመራር "5ቱ ማ"ዎች እና "የስሜት ብልህነት"ዙሪያ ለአንድ ቀን ሲሰጥ የነበረው ስልጠና
ተጠናቀቀ ተሰጠ።
መስከረም 13 ቀን 2019 ዓም




No comments:
Post a Comment