#HMKI መስከረም 12 ቀን 2019 ዓም የስራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት በክልሉ ለሚገኙ ሴክተር ተቋማት፥ በከይዘን ፍልስፍና አመራር "5 ማ"ዎችን እና "የስሜት ብልህነት"ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
ስልጠናው ለንብረት ክፍል፣ መዝገብ ቤት እና ለሰው ኃይል ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ የስልጠናው ዓላማ፥ ብክነትን በመከላከል ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለመፍጠር እንዲሁም ስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence – EI) በተመለከተም ሰልጣኞች የራሳቸውና የሌሎችን ስሜት በመለየት፣ በመረዳት፣ በመቆጣጠር እና ስሜታቸውን በተገቢ መንገድ በመጠቀም ጤናማ ግንኙነትና ውጤታማ ውሳኔ መፍጠር እንድችሉ ለማድረግ የታለመ ስልጠና ነው። ስልጠናው በቀጣይም ለሌሎች ተቋማት የሚሰጥ ይሆናል።
No comments:
Post a Comment