ሀዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም #HMKI በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት በጅግጅጋ ከተማ የሚከበረው 18ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓልን አስመልክቶ በሀረሪ ህዝብ ክልል መንግስት የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት ሠራተኞች ኢፌዴሪ ህገ መንግስትን በተመለከት በተዘጋጀው የጥያቄና መልስ ውድድር ፕሮግራም አካሄዱ።
በፕሮግራሙ
የተገኙት የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ በርሃኑ ሑንዴ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በዓሉ ሕዝቦች እኩልነታቸውን፣ አንድነታቸውንና ወንድማማችነታቸውን የሚያጠናክሩበት፥ ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሚያንፀባርቁበት፣ ማንነታቸው በሚገባ ያልታወቀላቸው ሕዝቦች እሴቶቻቸውን በአደባባይ የሚያስተዋውቁበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም በሱማሌ ብሔራዊ ክልል አዘጋጅነት በጅግጅጋ ከተማ የሚከበረው የ18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮችና ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በሚመለከት በክልሉ ለሚገኙ የመንግስት ተቋማት ሠራተኞች የተዘጋጀ
የህገ መንግስት የጥያቄና መልስ ውድድር በየተቋማቱ በማዘጋጀት የህገ መንግስት ግንዛቤን ለማጎልበት እና በዓሉን
ለመታደም ወደ ጅግጅጋ ለሚጓዙ ታዳሚዎች በክልላችን በሚያልፉበት ጊዜ የክልሉ ህዝብ እና የመንግስት ሠራተኛው የዕንግዳ ተቀባይነቱን
በተግባር ማሳየት እንዳለበት በመግለፅ ዝግጅቱ መከፈቱን አብስረዋል።
በፕሮግራሙ መሰረት በተዘጋጀው የጥያቄና መልስ ውድድር ሦስት የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች
የተወዳደሩ ሲሆን፣ የውድድሩ አሸናፊ ለሆኑት ተሳታፊዎች የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
የዘንድሮው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ከኅዳር 25 እስከ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ
"ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በጅግጅጋ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር
ይጠበቃል፡፡
Comments
Post a Comment