Wednesday, November 8, 2023

የ2016 በጀት፣ የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ

 "2016 በጀት 1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ"


#HMKI ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እንዲሁም የታዩ ጉድለቶችን ለማረም በሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና የተገኘን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ወደ ተግባር በመቀየር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሠራተኛ ኃላፊነቱን በመወጣት ጠንክሮ መስራት እንዳለበት ተገለፀ። 

መጀመሪያ የኢንስቲትዩቱን 2016 በጀት ዓመት መደበኛ ዕቅድ 1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ጋር በመሆን የገመገመ ሲሆን፣ በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጉድለቶችን እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን፣ በመገምገም በቀጣይ ሊስተካከሉ የሚገባቸውን በመለየት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እንዲሁም የታዩ ጉድለቶችን በማረም የተሻለ የአፈጻጸም ውጤት ለማምጣት ሁሉም ሰራተኛ ተቀናጅቶ በቡድን ስሜት መስራት እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል።

በመጨረሻም ጥቅምት 28/2016 የቡድን ሥራ (Team Building) በስልጠናው የተገኘውን እውቀት፣ ክህሎትና ባህሪን በማቀናጀት በቀጣይ በቡድን ሥራ በመመራት የተሻለ የአፈፃፀም ለማስመዝገብ መላው የተቋሙ ሠራተኛ መስራት እንደሚገባ እና በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጠንካራ አፈፃፀምን በማስቀጠል እና ደካማ ጎኖች ለማረም የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ፣ ጥቅምት 27-28 ቀን 2016 ዓም ለሁለት ቀን ሲካሄድ የነበረው የአፈፃፀም ግምገማና ሲሰጥ የነበረው አቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ።



No comments:

Post a Comment

የ5ቱ “ማ” ዎች ትግበራ በድሬ ጠ ያራ ወረዳ  #HMKI ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም፡ የስራ ቦታ ፅዱ፣ ጉዳት የማያደርስ እና ምቹ እንዲሆን፣ የስራ እርካታ እንዲኖር እንዲሁም በስራ ላይ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የ...