Friday, September 1, 2023

"የመሸኛ እና “የእንኳን ደህና መጡ” ፕሮግራም (Farewell and Welcome Program)

 #HMKI ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም


ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ እና ማኔጅመንትና ካይዘን ኢንስቲትዩት የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች “የመሸኛ" እና “የእንኳን ደህና መጡ” ፕሮግራም አካሄዱ። 

ቀደም ሲል የክልሉ መንግስት በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የተለያዩ ዘርፎች የአመራር ሽግሽግ ማድረጉ ይታወሳል።


በዚሁ መሰረት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የነበሩ ክብርት ወ/ሮ ፈሪሃ መሀመድን የሴቶች ወጣቶችና ሕጻናት ቢሮ ኃላፊ፣ በተመሳሳይ የሴቶች ወጣቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን ክብርት ወ/ሮ ደሊላ ዩሱፍ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ 

ይህን መሰረት በማድረግ በሁለቱ ተቋማት ሰራተኞችና ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ቀደም ሲል የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ለነበሩ ክብርት ወ/ሮ #ፈሪሃ_መሀመድ "#የሽኝት" ፕሮግራም እንዲሁም ለክብርት ወ/ሮ #ደሊላ_ዩሱፍ "#የእንኳን_ደህና_መጡ" ፕሮግራም በቢሮው እና በኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በደማቅ ስነስርዓት ፕሮግራሙ ተከናውኗል።

No comments:

Post a Comment

  🚦 ለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በስሜታዊ ብልህነት ስልጠና መስጠት ተጀመረ #HMKI መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ለትራፊክ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በ“ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligen...