ሀዳር 1 3 ቀን 2016 ዓ.ም #HMKI በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት በጅግጅጋ ከተማ የሚከበረው 18 ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓልን አስመልክቶ በ ሀረሪ ህ ዝብ ክ ልል መንግ ስ ት የሥራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት ሠራተኞች ኢፌዴሪ ህገ መንግስትን በተመለከት በተዘጋጀው የጥያቄና መልስ ውድድር ፕሮግራም አካሄዱ። በፕሮግራሙ የተገኙት የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ በርሃኑ ሑንዴ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በዓሉ ሕዝቦች እኩልነታቸውን፣ አንድነታቸውንና ወንድማማችነታቸውን የሚያጠናክሩበት፥ ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሚያንፀባርቁበት፣ ማንነታቸው በሚገባ ያልታወቀላቸው ሕዝቦች እሴቶቻቸውን በአደባባይ የሚያስተዋውቁበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በሱማሌ ብሔራዊ ክልል አዘጋጅነት በጅግጅጋ ከተማ የ ሚከበረው የ18ኛው የኢትዮጵ ያ ብሔሮችና ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ን በሚመለከት በክልሉ ለሚገኙ የ መንግስት ተቋማት ሠራተኞች የተዘጋጀ የህገ መንግስት የጥያቄና መል ስ ውድድር በየተቋማቱ በማዘጋጀት የህገ መንግስት ግንዛቤን ለማጎልበት እና በዓሉን ለመታደም ወደ ጅግጅጋ ለሚጓዙ ታዳሚዎች በክልላችን በሚያልፉበት ጊዜ የክልሉ ህዝብ እና የመንግስት ሠራተኛው የዕንግዳ ተቀባይነቱን በተግባር ማሳየት እንዳለበት በመግለፅ ዝግጅቱ መከፈቱን አብስረዋል። በፕሮግራሙ መሰረት በተዘጋጀው የጥያቄና መልስ ውድድር ሦስት የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች የተወዳደሩ ሲሆን፣ የውድድሩ አሸናፊ ለሆኑት ተሳታፊዎች የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል። የዘንድሮው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ከኅዳር 25 እስከ 29 ...