5ቱን "ማ" ዎች መተግበር /Implementing the 5S/


5ቱን "ማ" ዎች መተግበር /Implementing the 5S/


  1.  ማጣራት (Sort) 

  • የሚያስፈልጉ ነገሮችን (ቁሳቁስ "መረጃ" ዶክመንቶችን ወ.ዘ.ተ.) ከማያስፈልጉት መለየትና የማያስፈልጉትን ማስወገድ፣
  • የማያስፈልጉና መወገድ የሚገባቸውን ነገሮችን ለመለየት የሚያስችል መስፈርት ማዘጋጀት፣
  • የማያስፈልጉ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ወይንም ቀድሞ ከተከማቹበት ስፍራ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ማድረግ ይገባል፣

    2. ማስቀመጥ (Set in Order)

        

  • የማጣራት ሂደት ማንኛውንም ዓይነት ንብረት በቀላሉ ለማግኘትና ለአያያዝ አመቺ እንዲሆን የሚያስችል የክምችት ክፍል (መጋዘን) ማዘጋጀትን እንዲሁም አመቺ ሥፍራና አቀማመጥ (layout) መምረጥና በአግባቡ መደርደርን ይመለከታል፡፡

  • የክምችት ክፍልና በአግባቡ መጠቀም ተገቢ ሲሆን "ለማንኛውም ነገር ተገቢውን ሥፍራ ማዘጋጀት፤ ለዚሁ በተዘጋጀው ሥፍራም (ሌላ ምንም ነገር ያለማስቀመጥ) ተገቢውን ነገር ማስቀመጥ" የሚለውን መርህ መከተል ያስፈልጋል፡፡

    3.ማፅዳት (Shine)

 

          የሥራ ቦታችንንም ሆነ የሥራ መገልገያ መሣሪያዎች /ቁሣቁሶችን ማፅዳት ሲባል፡-
  • ማንኛውንም ዓይነት ቆሻሻ፣ አቧራና እንግዳ የሆኑ ነገሮች በአግባቡ ማጽዳትን እንዲሁም የሥራ ቦታንና ቁሳቁሶችን ጽዱ ከማድረግ ባለፈ ቀድሞውኑ ሊፈጠር ከሚችል ብልሽት /አደጋ ችግሮችን በማየት የመፈተሽ (inspection) ሥራ ማከናወንን ይጨምራል፣
  • የሥራ ቦታችንን /ቁሳቁሶችን ከማንኛውም የቆሻሻ ጠብታ /ጥቃቅን ብልሽቶች፣ ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀም ወዘተ... ችግሮች ካሉ የማየትና ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡ በዚህም ሂደት (ለምሳሌ፡- የአቧራ፣ የማፍሰስ /የማንጠባጠብ ችግሮች ወዘተ...) ከወዲሁ በማስተዋል ዋንኛ የችግሩ ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በመለየት ሊደርስ ይችል የነበረውን ከፍተኛ ጉዳት ለማስቀረት የሚያስችል የመከላከል እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡

    4. ማላመድ /Standardization/

 
  • ማላመድ ማለት 5ቱን "ማ"ዎች ለመተግበር በተቋሙ ውስጥ የተመሰረቱትን ቡድኖች ሊያግዝ የሚችል የጋራ ስምምነትን በትግበራ ወቅት በሰነድነት እንዲያገለግላቸው ማስቻልና በ5ቱም "ማ"ዎች ትግበራ የሚከናወኑ ሥራዎች በምን ደረጃ (ስታንዳርድ) መፈፀም እንደሚገባቸው ደንብና መመሪያዎችን በትክክል በማስቀመጥ በዚሁ መሠረት መፈፀማቸውን ለመከታተል እንዲያስችል ከወዲሁ ማመቻቸትን ይመለከታል፡፡

    5. ማዝለቅ /Sustain/

  • ማዝለቅ የካይዘን ትግበራ ቡድኑ አባላት በተመረጠው የሥራ አካባቢ ለማከናወን የተስማሙባቸው 5ቱን "ማ"ዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲፈጸሙ የሚያግዝ ሂደት ነው፣

  • ይህ የማዝለቅ ሂደት 5ቱን "ማ"ዎች በመተግበር ሂደት ማንኛውም ሰው በራሱ የአሠራር መመሪያው አድርጎ በመውሰድና በማላመድ እየሠራበት መቀጠሉን ለማረጋገጥ ያግዛል፡፡

 

Post a Comment

1 Comments