ካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ስልጠና #HMKI ከታህሳስ 18 ቀን 2016፡ ካይዘን አመራር ፍልስፍና ስልጠና የትምህርት ተቋማትን ምቹ ስራ ቦታ በመፍጠር የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያሻሽል መሆኑ ተገለጸ ። የሀረሪ ክልል ስራ አመራርና ከይዘን ኢንስቲትዩት ከሀረሪ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በካይዘን አመራር ፍልስፍና ዙሪያ በክልሉ ለሚገኙ የ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና ንብረት ክፍል ኃላፊዎች በኢንስቲትዩቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከታህሳስ 18-19 /2016 ዓም) ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።