#HMKI ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃ ብት ልማት ቢሮ እና ማኔጅመንትና ካይዘን ኢንስቲትዩት የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች “ የመሸኛ" እ ና “ የእንኳን ደህና መ ጡ” ፕሮግራም አካሄዱ። ቀደም ሲል የክልሉ መንግስት በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የተለያዩ ዘርፎች የአመራር ሽግሽግ ማድረጉ ይታወሳል። በዚሁ መሰረት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የነበሩ ክብርት ወ/ሮ ፈሪሃ መሀመድን የሴቶች ወጣቶችና ሕጻናት ቢሮ ኃላፊ፣ በተመሳሳይ የሴቶች ወጣቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን ክብርት ወ/ሮ ደሊላ ዩሱፍ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ ይህን መሰረት በማድረግ በሁለቱ ተቋማት ሰራተኞችና ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ቀደም ሲል የ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ለ ነበሩ ክብርት ወ/ሮ #ፈሪሃ_መሀመድ "#የሽኝት" ፕሮግራም እንዲሁም ለ ክብርት ወ/ሮ #ደሊላ_ዩሱፍ "#የእንኳን_ደህና_መጡ" ፕሮግራም በቢሮው እና በኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በደማቅ ስነስርዓት ፕሮግራሙ ተከናውኗል።